የኢትዮጵያ ህዝብ ቆጠራ - የአሁኑ አመት ትንበያ
የኢትዮጵያ ህዝብ ቆጠራ መረጃን እና የህዝብ ብዛት ትንበያ በክልል፣ በዞን፣ እና በወረዳ ይዳስሱ።
 • ኢትዮጵያ
 • 96,543,226 የህዝብ ብዛት
 • 85.66% 82,696,831 የገጠር ህዝብ ብዛት
 • 14.34% 13,846,395 የከተማ ህዝብ ብዛት
 • 50.05% 48,317,441 የሴት ህዝብ ብዛት
 • 49.95% 48,225,785 የወንድ ህዝብ ብዛት
ፈጣን እውነታዎች

ይህ ድህረገፅ የአውሮፓውያንን የቀን አቆጣጠር ይጠቀማል። ከ1994 እስከ 2021 ለቀረቡት ትንበያዎች ቀመሩ የ2007 የወሊድ እና የሙት መጠንን መሠረት ያደረገ ነው። ፍልሰት የትንበያዎቹ ቀመር ላይ አልተካተተም።

በህዝቦች ወደከተማ የመፍለስ አዝማሚያ፣ የከተሞች ቁጥር ከትንበያው እንደሚበልጥ ይጠበቃል።

በ2007ቱ የህዝብ ቆጠራ፣ የሶማሌ ክልል ባልተለመደ ሁኔታ ከፍ ያለ የህፃናት ሞትን አስመዝግቧል። እናም የክልሉ እውነተኛ የህዝብ ቁጥር ከተተነበየው እንደሚበልጥ ይጠበቃል።

የህዝብ ብዛት በክልል
የህዝብ ብዛት በዕድሜ ክልል

የትንበያ ዘዴ

ከ1994 መረጃ በመነሳት የ1999 የህዝብ ብዛትን ለመተንበይ የተወሰዱት ዘዴዎችና ይሆናልታዎች ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል።

 • የ2007 የህዝብ ቆጠራ ላይ የቀረቡት የሙት እና የወሊድ መጠኖች ለሁሉም ዓመታት የትንበያ ቀመሮች አገልግለዋል።
 • የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የህዝብ ብዛት ቁጥሮችን፣ የወሊድ መጠንን፣ እና የሙት መጠንን የሚያሳትመው በ5 አመት ክልል (0-4, 5-9, 10-14, ..., 90+) ነው። በመሆኑም ለቀመሮቹ፣ የ5 አመት ክልል እንደዋና መነሻ ሆኖ ተወስዷል።
 • የ1999 ከ25-29 የዕድሜ ክልል ህዝብ ብዛትን ለመተንበይ የ1994 ከ20-24 የዕድሜ ክልል ህዝብ ብዛት ላይ በ5 ዓመታት ውስጥ የሞቱትን መቀነስ ነው። የሙት መጠኑ በየዓመቱ ይቀያየራል። ቢሆንም የለውጡ ለውጥ አይቀያየርም የሚል ይሆናልታ ተወስዷል። ይህ ማለት የሙት መጠን በ20-24 የዕድሜ ክልል ባሉት ጀምሮ ቀስ እያለ በመቀነስ ወይም በመጨመር በ25-29 ዕድሜ ክልል ባሉት የሙት መጠን ይደርሳል። ለእያንዳንዱ ወረዳ የከተማ ሴት፣ የከተማ ወንድ፣ የገጠር ሴት፣ እና የገጠር ወንድ የሙት መጠኖች ለየብቻቸው ተሰልተዋል።
 • ከላይ ያሉት ይሆናልታዎች ለሁሉም ዕድሜ ክልል ማለትም ከ5-9 ጀምሮ እስከ 90+ ላሉት ቀመሮች ተወስደዋል።
 • የ0-4 የዕድሜ ክልል የ1999 የህዝብ ብዛትን ለማስላት ቀላል የሚባል አይደለም። በተጨማሪም ትክክለኛነቱ በትንበያው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው።
 • ከ1994 እስከ 1999 የሚወለዱት የ1999 የህዝብ ብዛትን የ0-4 ዕድሜ ክልል ይፈጥራሉ። በየዕድሜ ክልሉ ያሉ ሴቶች የሚወልዱት መጠን የሚሰላው ለየብቻው ነው። በየዓመቱ በያንዳንዱ የዕድሜ ክልል የሚገኙ የሴቶች ህዝብ ብዛት ይቀንሳል። ቢያሳዝንም የተወሰኑት ስለሚሞቱ ማለት ነው። በተጨማሪም ቢያሳዝንም በየዓመቱ ከሚወለዱት ውስጥ የተወሰኑት ይሞታሉ። የወሊድ እና የሙት መጠኖች ሁለቱም በየአመቱ ይለዋወጣሉ። ነገር ግን የለውጡ ለውጥ አይቀያየርም የሚል ይሆናልታ ተወስዷል። ቀመሩ ለሚወለዱት ሁለቱም ፆታዎች ለየብቻው ተሰርቷል። ምንም እንኳን የወሊድ እና የሙት መጠኖች የተሰጠው በዞን ቢሆንም ቀመሩ ለእያንዳንዱ ወረዳ ለየብቻው ተሰርቷል።